በሀገር በቀል መድኃኒት ዙሪያ የሚመክር ጉባኤ በጂንካ ተጀመረ

72

 ኢዜአ ታህሳስ 11 / 2012 በሀገር በቀል መድኃኒትና ባህላዊ የፍትህ ስርዓት ዙሪያ የሚመክር ሀገር አቀፍ ጉባዔ ዛሬ በጂንካ ከተማ ተጀመረ፡፡ ጉባኤው የተዘጋጀው በባህልና ቱርዝም ሚኒስቴር፣  በደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና በጂንካ ዩኒቨርሲቲ ትብብር ነው።

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ቡዘና አልከድር  ጉባኤውን ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ ለሀገር በቀል ሀብቶች ትኩረት ባለመሰጠቱ ከዘርፉ ተገቢው ጥቅም እየተገኘ አይደለም፡፡

ሀገር በቀል መድኃኒትና ባህላዊ ፍትህ ስርዓት ለሀገር ግንባታ ትልቅ አስተዋጽኦ ያላቸው በመሆኑ ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ተናግረዋል።

ባህላዊ መድኃኒት ለሳይንሳዊ የመድኃኒት ቅመማ እንዲሁም ባህላዊ ፍትህ ስርዓት ለዘመናዊ የፍትህ ስርዓት ዕድገት የማይተካ ሚና እንዳላቸው አመላክተዋል ።

በጉባኤው በሀገር በቀል መድኃኒቶችና የግጭት አፈታት ነባራዊ ሁኔታን የሚያመላክቱ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይትና የባህላዊ መድኃኒት አውደ-ርዕይ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

በጉባኤው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር እንዲሁም የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ፣ የዘርፉ ምሁራንና የመገናኛ ብዙሃን አካላት እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም