የፕሪሚየር ሊግ የአራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች በመርሃ ግብራቸው መሰረት ይካሄዳሉ

94

ኢዜአ፤ታህሳስ 10/2012 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁሉም ጨዋታዎች ነገ እና ከነገ በስቲያ ከቀኑ በዘጠኝ ሠዓት ይካሄዳሉ።

የሊጉ የ2012 የአራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገ ሰባት  ሲካሄዱ ቀሪው አንድ ጨዋታ ከነገ በስትያ እሑድ ይካሄዳል።

በነገው መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ስታዲየም ቅዱስ ጊዮርጊስ ስሁል ሽረን ያስተናግዳል።

ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲም በትግራይ ስታዲየም ከጅማ አባ ጅፋር ይጋጠማል።

ሲዳማ ቡና በይርጋለም ስታዲየም መቀሌ ሰባ እንደርታን፣ ባህርዳር ከተማ በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ድሬድዋን፣ ፋሲል ከነማ ፋሲለደስ ላይ ሀድያ ሆሳዕናን ያስተናግዳሉ።

አዳማ ከተማ በአበበ በቂላ ስታዲየም ከወላይታ ድቻ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

በዚህ ዓመት ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የተቀላቀሉት ወልቂጤ ከተማና ሰበታ ከተማ ነገ /ቅዳሜ/ ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል ናቸው።

የፕሪሚየር ሊጉ ቀሪ አንድ ጨዋታ እሑድ የሚካሄድ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡናና ሀዋሳ ከተማ በአዲስ አበባ ስታዲየም ይገናኛሉ።

የሊጉ የውድድር ስነ ስርዓት ኮሚቴ የውድድር ባለሙያው አቶ ጋሻው ረታ በመርሃ ግብሩ መሰረት ሁሉም ጨዋታዎች ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት እንደሚካሄዱ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም