ፈረንሳይ ጅሃዲስቶችን ለመውጋት ሰው አልባ የጦር አውሮፕላኖችን እንደምታዘምት አስታወቀች፡፡

77
ታህሳስ 10/2012 ፈረንሳይ በአፍሪካ የሳህል ቀጠና  ጅሃዲስት ለመዋጋት  ሰው አልባ  የጦር አውሮፕላኖችን እንደምታሰማራ ማስታወቋን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ የሃገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር ፍሎሬንስ ፓርሊ እንዳሉትም ቅኝት ያደርጋሉ ተብለው የሚጠበቁት አሜሪካ ሰራሽ ሰው አልባ አውሮፕላኖችም በዋናነት የስለላ ስራዎችን ያከናውናሉም ተብሏል፡፡ በቀጠናው የሚሰማሩት እንያንዳንዱ ሰው አልባ የጦር አውሮፕላን ሁለት ግዙፍ በቆዳ የተሸፈኑ ቦንቦችን እንደሚሸከሙም ተገልጿል፡፡ ፈረንሳይ ከዚህ ቀደም ስትጠቀማቸው የነበሩ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በሳህል ቀጠና ያለውን ሁኔታ ለመከታተል ብቻ አላማ አድርገው ይንቀሳቀሱ እንደነበርም ዘገባው አስታውሷል፡፡ ሃገሪቱም ከ4ሺ በላይ ወታደሮቿን በቀጠናው በማሰማራት እስላሚክ ሽምቅ ተዋጊ አማፂያንን ለመዋጋት ለሰባት ዓመታት ያክል ተከታታይ ዘመቻ እያደረገች ትገኛለች፡፡ ባለፈው ወር ላይ በማሊ ባጋጠመ የሂሊኮፕተር መከስከስ አደጋ 13 የፈረንሳይ ወታደሮች ህይወታቸው ማለፉንም ዘገባው ጠቁሟል፡፡ የምዕራባዊን ሃይሎች በቅርቡ  እንዳሳቁትም የምዕራብ አፍሪካ መንግስታት በሳህል ቀጠና የሚንቀሳቀሰውን ጅሃዲስት አማፂ ብድኖን ለመዋጋት የሚያደርጉት ጥረት በቂ አለመሆኑን በመጠቆም ፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም