የአፋር ህዝብ ፍትሐዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የአራት ፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት የሆነውን መድረክን ተቀላቀለ

84

ኢዜአ ታህሳስ 8/ 2012 የአፋር ህዝብ ፍትሐዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የአራት ፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት የሆነውን መድረክ ፓርቲን ዛሬ በይፋ ተቀላቅሏል።

ፓርቲው ከመድረክ ጋር ለመቀላቀል የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ዛሬ ተፈራርሟል።

ስምምነቱን የፈረሙት የአፋር ህዝብ ፍትሐዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ መሐመድ ዳውድ እና የመድረክ ፓርቲ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ናቸው።

መድረክ ፓርቲ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ፣ የአረና ትግራይ፣ የሶሻል ዴሞክራሲ ፓርቲ እና የሲዳማ አርነት ንቅናቄን አቅፎ የያዘ ነው።

የአፋር ህዝብ ፍትሐዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲም መድረክን የተቀላቀለ አምስተኛ የፖለቲካ ፓርቲ ሆኗል።

የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ መሐመድ ዳውድ ፓርቲያቸው ከመድረክ ጋር ግንባር በመፍጠር ለህዝቦች እኩልነትና ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እንደሚሰራ በስነ-ስርዓቱ ላይ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም