የጎልድ ውሃ ማህበራዊ ሃላፊነትን በጠበቀ መልኩ ስራ መጀመሩ ይፋ አደረገ

82

ታህሳስ 7/2012 የጎልድ ውሃ ማህበራዊ ሃላፊነትን በጠበቀ መልኩ ከ300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ስራ መጀመሩን ይፋ አደረገ። ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት በኦሮሚያ ክልል በቡራዩና በአምቦ ስራ መጀመሩን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ በሱፍቃድ ካሳዬ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቀዋል።

ድርጅቱ የአካባቢ አየር ንብርት በጠበቀ መልኩና  ከ300 በላይ የሚሆኑ ሰራተኞችን በመቅጠር በሰዓት 170 ሺህ  የታሸገ ውሃ ለማምረት ዝግጅቱን አጠናቆ ስራ መጀመሩ ተገልጿል።

ድርጅቱ 85  በመቶ የአካባቢውን ማህበረሰብ የስራ እድል እንዲያገኝ አድርጎታል፤ አቅሙን በማሳደግ ምርቱን በአገር ውስጥ እንዲሁም ወደ ውጪ አገር  በሳውዲ አረቢያና በተባሩት አረብ ኤምሬትስ ምርቱን እንደሚያከፋፍል ጠቁመዋል።

አመራረቱና አስተሻሸጉ  ከአሜሪካ፣ ከጀርመንና ከሌሎች የተሻለ ተሞክሮ አላቸው ከተባሉ አገሮች የተወሰደ በመሆኑ የተሻለ ምርት እንደሚመረት በመግለጫው ተጠቅሷል።

ድርጅቱ የአየር ንብረትን በማይበክል መልኩእንደሚያመርትም ስራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

የምርቱ ማሸጊያዎች ተሰብስበው ለሌላ ጥቅም እንዲሰጡ የሚደረግ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ድርጅቱ የሚያመርታቸው ምርቶች ጥራታቸው ተጠብቆ በአማካኝ የገበያ ዋጋ ለተጠቃሚው ህብረተሰብ እንደሚቀርቡ ገልፀዋል።

 ከዚህ በፊት  20  የሚሆኑ ህፃናት የኩላሊት እጥበት ህክምና እንዲያገኙ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገው ድርጅቱ በተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶች በመሳተፍ የተሻለ ህብረተሰብ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት የድርሻውን ለመወጣት መዘጋጀቱም ተነግሯል።

የጎልድ ድርጅት ከዚህ በፊት ለስድት አመታት በማኒፋክቸሪግ፣በኮንስትራክሽን፣ በሪልስቴትና ሆስፒታሊቲሲሰራ የቆየ መሆኑ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም