በመቀሌ 70 እንደርታና ኢትዮጵያ ቡና አቻ ተለያዩ

61
ኢዜአ ታህሳስ 05/201--- በኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት መቀሌ 70 እንደርታ ዛሬ በሜዳው ኢትዮጵያ ቡናን አስተናግዶ አንድ እኩል ተለያየ። በሁለቱም ቡድኖች መካከል ተመጣጣኝ ፍክክር የታየበት ጨዋታ ነበር። ከእረፍት በፊት በስምንተኛው ደቂቃ መቀሌ 70 እንደርታ በአሸናፊ ሃፍቱ ቀዳሚ የሚያደረገው ግብ ማስቆጠር ችሏል። ኢትዮጵያ ቡና አቻ የምታደረገውን ግብ ደግሞ በ15ኛው ደቂቃ ላይ በእንዳለ ደባልቄ አማካኝነት አስቆጥሯል። በሁለተኛው አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ለመሸናነፍ ያደርጓቸው የግብ ሙከራዎች ጎልተው የታዩበት ባለመኖሩ በአቻ ውጤት ተለያይተዋል። የመቀሌ 70 እንደርታ አሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይለ በሰጡት አስተያየት “ከእረፍት በኋላ ለማጥቃት ሞክርን ብንጫወትም ተጫዋቾቻችን የስነ ልቦና ጫና ስለነበራቸው አቻ ወጥተናል “ብለዋል። የቡናው አሰልጣኝ ካሳሁን አራጌ በበኩላቸው “አሸንፈን ለመውጣት ተጫውተን  በማጥቃት በኩል ደካማ እንቅስቃሴ በማድረጋችን አቻ ብንለያየም የምንፈልገው ውጤት ነው”ሲሉ ገልጸዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም