ዓለም አቀፍ ውጤቱን ማስጠበቅ እንደሚገባ ተገለፀ

75
ኢዜአ ታህሳስ 3/2012 ሠላምና አብሮነትን በማስቀጠል በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካይነት የተገኘውን ዓለም አቅፍ ውጤት ማስጠበቅ እንደሚገባ ተገለፀ ፡፡ ሠላምና አብሮነትን በማስቀጠል በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካይነት የተገኘውን ዓለም አቅፍ ውጤት ማስጠበቅ እንደሚገባ ተገለፀ ፡፡ ጠቅላይ ሚኒሰትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ያገኙት የዓለም የሠላም ኖቤል ሽልማት አስመልክቶ በሀዋሳ ከተማ የደስታ መግለጫ መርሀ-ግብር ተካሄዷል ፡፡ በደስታ መግለጫ መርሀ-ግብሩ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ  ይህንን ሽልማት ማግኘታቸው ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካ ኩራት ነው፡፡ እንዲሁም ዶክተር ዐብይ የሀገራቸውን ስምና ዝናን ከፍ ማድረጋቸው ገልፀው ሽልማቱ የመላው ኢትዮጵውያን እንደሆነም አስረድተዋል ፡፡ ሽልማቱን የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎችና የአካባቢው ህዝቦች በታላቅ ክብርና አድናቆት የሚቀበሉት እንደሆነ የተናገሩት አቶ ጥራቱ ከተማዋ የፍቅር ፣ የአብሮነትና የሠላም መሆኗን ለማስቀጠል አቅም የሚሆነን በመሆኑ ውጤቱን የማስጠበቅ ኃላፊነት አለብን ብለዋል ፡፡ በመርሀ-ግብሩ ከተገኙ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች መካከል ባሻ ጋቢሳ ሙለታ ጠቅላይ ሚኒስትር ደክተር ዐብይ አህምድ የዓለም የሠላም ኖቤል ተሸላሚ በመሆናቸው ደስታው የእሳቸው ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵውያን ብሎም የአፍሪካዊያን ጭምር ነው ብለዋል ፡፡ ሽልማቱ የሠላም እንደመሆኑ ኢትዮጵያ ሠላም ሆና እንድትቀጥል ትውልዱም የሠላምን መንገድ እንዲከተል ማድረግ የሚጠበቅባቸው መሆኑንም ገልፀዋል ፡፡ ወይዘሮ አልማዝ ሀፍቱ በበኩላቸው ዶክተር ዐብይ አህመድ ባገኙት ሽልማት እጅግ መደሰታቸውን ገልፀው በቀጣይም ከጎናቸው ነን ብለዋል ፡፡ ተማሪ አሸናፊ ደገፉ ደግሞ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ባገኘችው ድል ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማው ገልጿል፡፡ እኛም ጥሩ ሥራ ሰርተን ሀገራችንን ከፍ ለማድረግ እንድንነሳሳ ዶክተር ዐብይ መልካም ምሳሌ ሆነውናልም ብሏል ፡፡ በደስታ መግለጫ መርሀ-ግብሩ የሀዋሳ ከተማ አመራር አካላት ፣ ነዋሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ ትምህርት ቤት የተውጣጡ ተማሪዎች ተገኝተዋል ፡፡      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም