በጀኔራል ኻሊፋ ሃፍታር የሚመራው ጦር የትሪፖሊ ከተማ ን በቁጥጥር ስር ለማዋል  ጦሩንእንደሚያዘምት አስታወቀ

86

ኢዜአ፤ ታህሳስ 3/2012 በተባባሩት መንግስታት ድርጅት ድጋፍ የሚደረግለት  የሊቢያ መንግስት መቀመጫ  የሆነችውን ትሪፖሊ  በቁጥጥር ስር ለማዋል  ጀኔራል ኻሊፋ   ሃፍታር ትዕዛዝ ማስተላለፈቸው  ተገልጸዋል፡፡

በተባበሩት መንግስታት የሚደገፈውን መንግስት ጠራርጎ በማስወጣት ዋና ከተማዋ  ትሪፖሊን  ለመቆጣጠር ምንም ዓይነት የምናባክነው ግዜ የለንም ብሏል ጀነራል ካሊፋ ሃፍታር ፡፡

ጀኔራል ኻሊፋ ሃፍታር  የሊቢያ ዋና ከተማ ትሪፖሊን ነጻ ለማውጣት የሚስችላቸውን ወሳኝ ውግያ ለማድረግ  ቅድመ ዝግጅት ማጠናቃቀቸውን ገልፀዋል፡፡

ጀኔራል ኻሊፋ ሃፍታር  ይህን ቢሉም በጀነራል ካሊፋ ሃፍታር ወታደሮች በኩል ተቃውሞ ሳይገጥሟቸው እንዳልቀረ ተገልጸዋል፡፡

እስከ አሁን  በአካባቢው  ምንም ዓይነት ወታደራዊ እንቅስቃሴ መኖሩን የሚያሳይ መረጃ  አልተገኘም ሲል የዘገበው አልጀዚራ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም