የሰላም ሎሬት ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ አቀባበል ተደረገላቸው

125
ኢዜአ፤ ታህሳስ2/2012 ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ የ2019 የኖቤል ሰላም ተሸላሚ በመሆናቸው ዛሬ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ደማቅ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ 2019 የኖቤል የሰላም ተሸላሚ በመሆን ሽልማታቸውን ከትናንት በስቲያ በኖርዌይ ኦስሎ በተካሄደ ደማቅ ስነ ስርዓት መቀበላቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ በኖቤል ኢንስቲትዩት የክብር መዝገብ ላይ በአማርኛ የተጻፈ ፊርማ በማኖር የመጀመሪያው መሆናቸውንም ኢንቲትዩቱ መረጃ አውጥቶ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ አዲስ አበባ ሲደርሱ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ አባ ገዳዎች ፣ታዋቂ ግለሰቦች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ለክብራቸውም 21 ጊዜ መድፍ ተተኩሷል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም