የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኖቤል ሽልማት በዓለም መገናኛ ብዙሃን እይታ

104
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሰላም ኖቤል ሽልማታቸውን ከተቀበሉ በኋላ የተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ምን አሉ? ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ትናንት ሽልማታቸውን በኖርዌይ ርዕሰ መዲና ኦስሎ ተገኝተው ከተቀበሉ በኋላ በዓለማችን በርካታ የብሮድካስትና የህትመት ሚዲያዎች ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል። የእንግሊዙ የቴቪዥን ጣቢያ ቢቢሲ በዘገባው "ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ አዲስ የመነቃቃት መንፈስ የፈጠሩ መሪ" ሲል ሀተታውን ይጀምራል። በእርሳቸው ጠንሳሽነት እውን የሆነው “የመደመር” እሳቤና በመፅሐፍ መልክም የቀረበው አዲስ አተያይ በተለይ በኢትዮጵያ ሚዲያ ናኝቷል ብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገር ውስጥም ይሁን በቀጠናው አገራት በፈጠሩት አንፃራዊ መረጋጋትና ለሰላም ባላቸው ቁርጠኝነት የኖቤል ተሸላሚ መሆናቸውን ጠቅሷል ቢቢሲ በዘገባው። ዘገባው የጠቅላይ ሚኒስትሩን በርካታ ስኬቶችና እየተፈተኑባቸው ያሉ ተግዳሮቶችንም አካቷል። አልጀዚራም ዶክተር አብይ አህመድ ለረጅም ጊዜ እልባት ሳያገኝ የቆየውን የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ወደ ስልጣን እንደመጡ ጊዜ ሳያባክኑ ችግሩን በመፍታታቸው የሰላም ኖቤል ተሻላሚ ሆነዋል ሲል በሰፊው ዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁለቱ አገሮች ህዝቦች መካከል ሰላም በመፍጠር ያሳዩት ቁርጠኝነትና ያመጡት ውጤትም ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑንም አመላክቷል። በሁለቱ አገሮች መካከል በተደረገው ደም አፋሳሽ ጦርነትም ከ80 ሺህ በላይ ሰዎች መሞታቸውን ያስታወሰው ዘገባው፤ ጦርነቱ እስከ ወዲያኛው ተቋጭቶ ሰላምን ማምጣት ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ነውም ብሏል። ዶክተር አብይ ከሽልማታቸው በኋላ በኦስሎ ከተማ የስብሰባ አዳራሽ(City Hall) ባደረጉት ንግግርም ሽልማቱ ” የመላ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራዊያን በተለይም ለሰላም ሲሉ መስዋእትነት ለከፈሉ ሁሉ ነው” ማለታቸውን አልጀዚራ ዘግቧል። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህምድ የሰላም የኖቤል ሽልማታቸውን ከተቀበሉ በኋላ ባደረጉት ንግግር በምስራቅ አፍሪካ ሰላም እንድሰፍን ጥሪ አቀረቡ በማለት የዘገበው ደግሞ ሲ ኤን ኤን ነው። በንግግራቸው "የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ሃያላን አገሮች ወታደራዊ ይዞታቸውን ለማስፋት የሚሽቀዳደሙበት መሆን የለበትም" ማለታቸውንም አክሏል። በአካባቢው ሽብርተኞች የሽብር መረባቸውን ለመዘርጋትና ስራቸው ላይነቀል ለዘላለሙ ለመትከል እየታተሩ መሆኑን በስጋትነት መመልክታቸውን ሲ ኤን ኤን በዘገባው አካቷል። ዘ ግሎብ ኤንድ ሜይል የተባለው ድረ ገፅ በበኩሉ ዶክተር አብይ የሰላም ኖቤል ሽልማታቸውን በደማቅ ስነ ስርአት መቀበላቸውን ገልጿል። ሽልማታቸውን ከተቀበሉ በኋላ ባደረጉት ንግግርም የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የሽብርተኞች መናገሻ እንዳይሆን ስጋታቸውን ገልጸዋል ይላል። አካባቢው የአሸባሪዎች የስጋት ቀጠና መሆኑን ተከትሎ ሃያላን አገራት የበላይነት ለመያዝ አካባቢውን እየተቆጣጠሩት መሆኑንም አስምረውበታል ብሏል ዘ ግሎብ። ጠቅላይ ሚኒስትር ሎሬት አብይ ምስራቅ አፍሪካ የጦርነት አውድማ እንዲሁም "የሃያላን መፈታተኛ መድረክ መሆን የለበትም" ሲሉም አሳስበዋል ሲል ዘገባው አክሏል። “ጦርነትአስከፊነው፤ከ20ዓመትበፊትበባድሜየጦርነትአውደግንባርተሳትፌየብዙዎችህይወትሲቀማአይቻለሁኝ፤ከሰላምውጭአዋጭመንገድየለም” በማለትየአሁኑጠቅላይሚኒስትርእናየቀድሞውወታደርአብይአህመድከሰላምኖቤልሽልማታቸውበኋላንግግርማድርጋቸውንየዘገበውደግሞአይሪሽኢንድፐንደትነው። የራስን ሰላም እውን ለማድርግ የጎረቤትን ሰላም ማረጋገጥና ለሰላም አብሮ መስራት ግድ ነው ሲሉም አስረግጠዋል ብሏል። የጠቅላይሚኒስትርአብይንየሰላምኖቤልሽልማትንበማስመልከትእነዚህናሌሎችበርካታመገናኛብዙሃንበፊትገፆቻቸውሰፊሽፋንሰጥተውታል። በረዶዋማ የኦስሎ ከተማም የኢትዮጵያ መዲና እስክትመስል ድረስ በአትዮጵያ ባንዲራ ተሽቆጥቁጣ ማምሸቷን አለም ዋቢ ሆኗታል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም