የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች የእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ ማዕከልን ጎበኙ

71

ኢዜአ ታህሳስ 01/2012 የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ ማዕከል ጉብኝት እያደረጉ ነው።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ እና የቋሚ ኮሚቴዎች ሰብሳቢዎች፣ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ፣ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ብርቱካን አያኖን ጨምሮ ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ናቸው ጉብኝት እያደረጉ ያሉት።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ከቀናት በኋላ ኢትዮጵያ ወደ ህዋ    ስለምታመጥቃት የመሬት ምልከታ ሳተላይትና በእንጦጦ ስላለው የሳተላይቷ መቆጣጠሪያ ጣቢያ የስራ እንቅስቃሴ ገለፃ አድርገዋል።

የእንጦጦ ኦብዞርባቶሪ ማዕከል ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሳተላይት ማምጠቂያው ቀን ድረስ ለህዝብ ጉብኝት ክፍት እንደሚሆንም ተገልጿል።

ኢትዮጵያ ታህሳሰ 10 ቀን 2012 ዓ ም ማለዳ 12 ሰዓት ከ22 ደቂቃ የመሬት ምልከታ ሳተላይቷን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ህዋ ታመጥቃለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም