ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርስቲ የመጡበት ዓላማ ለማሳካት ሊሰሩ ይገባል

58
ኢዜአ ህዳር 30/2012 ተማሪዎችም የማንም የፖለቲካ መሳሪያ ሳይሆን ወደ ዩኒቨርስቲ የመጡበት ዓላማ ለማሳካት ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው ተመለከተ። የራያ ዩኒቨርስቲ ከማይጨው ከተማ ማህበረሰብ ጋር በመሆን የብሔር ብሐረሰቦች እና 15ኛው የሙስና ቀን በማይጨው ከተማ አከበረዋል። በበዓሉ ወቅት የማይጨው ከተማ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ  መምህርት ፍፁም ካሳሁን እንዳሉት በዓሉ የሚከበረው ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ይደርስባቸው ከነበረው ጭቆና ተላቆ ማንነታቸውን በአደባባይ የሚገልፁበት ህገ መንግስታዊ ስርዓት በመቋቋማቸው ነው። "ብዝሁነታችንና ልዩነታችን ውበታችን ከመሆኑ አልፎ  ለፖለቲካ ጥቅም ሲባል አንድነታችን እንዳይጠናከር አድርገዋል የሚል ትርክት አደጋ አለው" ብለዋል። የብሄሮች ብሄረሰቦች ስነ ልቦና የሚጎዳ አባባል   መቆም እንዳለበትም ጠቁመዋል። ተማሪዎችም ወደ ዩኒቨርስቲ የመጡበት ዓላማ እውቀት ለመሸመት እስከ ሆነ ድረስ የማንም የፖለቲካ መሳሪያ ሳይሆኑ ለትምህርታቸው ትኩረት መስጠት እንዳለባቸው አፈ ጉባኤዋ አመልክተዋል። በዩኒቨርስቲው የሁለተኛ ዓመት ተማሪ አሊ ሙስጠፋ በበኩሉ " በዓሉ የራስህንና የሌሎች ብሔሮች ባህል የምታስተዋወቅበት  በመሆኑ  ፋይዳ የጎላ ነው " ብሏል። ህገ መንግስቱ የሁሉም ብሔር ብሐረሰቦችና ህዝቦች  መብቶችን ዋስትና በመሆኑ ሳይሸራረፍ ተግባራዊ ሊሆን እንደሚገባውም አመልክቷል። በዩኒቨርስቲው የስነ ምግባር ባለሙያ ወይዘሮ ካህሱ ቦለድ ሙስና ጎጂ በመሆኑ ሁሉም ህብረተሰብ በጋራ ሊከላከለው እንደሚገባ አሳስበዋል። "ምንጩን ያልታወቀ ሀብት አንዱ ለሙስና መስፋፋት ምክንያት ስለሚሆን የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ሀብቱ ማስመዝገብ  እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም