የብሄር ብሄረሰቦች በዓል መከበር አብሮነታችንን ለማጠናከር ፋይዳው ከፍተኛ ነው… የበዓሉ ታዳሚዎች

96

ኢዜአ፤ ህዳር 29 /2012 የብሄር ብሄረሰቦች በዓል ስከበር ባህልን ከማስተዋወቅም በላይ አብሮነትን ለማጠናከር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን የበዓሉ ታዳሚዎች ተናገሩ፡፡

በ14ኛው የብሄር ብሄረሰቦች በአል በአዲስ አበባ ስታዲየም ሲያከብሩ ያገኘናቸው የበዓሉ ታዳሚዎች እንደጠቆሙት፤ በዓሉ ባህላቸውን ከማስተዋወቅ ባለፈ ለአንድነታቸውና ለአብሮነታቸው ያለው  ፋይዳ ቀላል አለመሆኑን ነው የጠቀሱት::

ከደቡብ ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን እንደመጣ የሚናገረው  በሮላ  ቦራቼ  የራሱን  ብሄረሰብ  አካባቢ ባህል የሚያንጸባርቁ  ልዩ ልዩ ጭፈራዎችን፣ አልባሳትና ባሀላዊ ምግቦችን ለማስተዋወቅ እድል እንደሚፈጥር ጠቁሞ የሌሎችን ባህል በማየትም ልምድ እንደሚቀስም ተናግሯል::

ከባህል ትውውቁ ባሻገር ብሄር ብሄረሰቦች በአብሮነት አንድነታቸውን የሚያጠናክሩበት መድረክ እንደሆነም በመጠቆም::

የመኢኒት ብሄረሰበን ባህል ሲያስተዋውቅ ያገኘነው አበበ ለገሰ፤ በአሉ የህዝቦችን አብሮነት የሚያሳይ በመሆኑ ለአንድነት ያለው ጠቀሜታ ቀላል አለመሆኑን ጠቅሶ የዘንድሮ በአል አንደሌላው ጊዜ ደማቅ አለመሆኑን ይናገራል፡፡

የቀቤና ተወካይ የሆኑት አቶ አበዱልጀሊል ተማም በበኩላቸው በዓሉ በየአመቱ ሲከበር ብሄር ብሄረሰቦች በአንድ መድረክ በመሰባሰብ አንድነቱንና አብሮነቱን የሚያሳይበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን መምጣታቸውን የገለጹ አቶ በዳሶ ቡታ በበኩላቸው፤ “ብዝሃነታችንን በዴሞክራሲያዊ መን ገድ መያዘ እና ማስተናገድ ይኖርብናል”በማለት በዓሉ ሁሉም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የሚወዱት እና በጉጉት ጠብቀው የሚያከብሩት እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም