የትግራይ ዓመታዊ የብስክሌት ውድድር ተጠናቀቀ

63
ኢዜአ፤ ህዳር ር 29/12 ዓ/ም በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ላለፉት ዘጠኝ ቀናት ሲካሔድ የሰነበተው የትግራይ ክልል ዓመታዊ የብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር በትራንስ ኢትዮጵያና በመስፍን ኢንዱስትርያል ኢንጂነሪንግ አሸናፊነት ተጠናቀቀ። በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ላለፉት ዘጠኝ ቀናት ሲካሔድ የሰነበተው የትግራይ ክልል ዓመታዊ የብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር በትራንስ ኢትዮጵያና በመስፍን ኢንዳስትርያል ኢንጂነሪንግ ተወዳዳሪዎች አሸናፊነት ተጠናቀቀ። ከህዳር 20 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በድምቀት ሲካሄድ በቆየው የብስክሌት ውድድር የመስፍን እንዱስርያል ኢንጂኔርንግ በሶስት የውድድር አይነቶች በማሸነፍ የሶስት ዋንጫዎች  ባለቤት ሆኗል ። ክለቡ  በክሮኖ ሜትር በኮርስ “ቢ” በሴቶች ፣ በከተማ የዙር ውድድር በኮርሶ”ኤ” እና በኮርሶ “ቢ”በሴቶች አሸነፊ ሆኗል፡፡ ትራንስ ኢትዮጵያ የብስክሌት ክለብ ደግሞ በክሮኖ ሜትር ኮርስ “ኤ” በሴቶችና በወንዶች በጎዳና የዙር ውድድር ኮርስ “ኤ” በወንዶች  አሸነፊ በመሆን ሶስት ዋንጫዎችን አግኝቷል ። የጉና ብስክሌት ክለብ በበኩሉ በክሮኖ ሜትር ኮርስ “ቢ” እና በጎዳና የዙር ውድድር ኮርስ “ቢ” ወንዶች በማሸነፍ ሁለት ዋንጫዎችን አንስቷል። በሁለቱም ፆታዎች አስራ ሁለት ወረዳዎች ተሳታፊ በሆኑበት ውድድር  ደግሞ በማውንቴን ብስክሌት ደጉዓ ተምቤንና ወቅሮ ከተማ በሁለቱም ጾታዎች አሸነፊ በመሆን እየንዳንዳቸው ሁለት ዋንጫዎችን አንስተዋል። ስድስት ክለቦች ተሳታፊ የሆኑበት የክሮኖ ሜትርና የጎዳና የዙር ውድድር ደግሞ በወንዶች ደስታ አልኮል ፋብሪካ ሁለት ዋንጫዎች አንስተዋል። በሴቶች የክሮኖ ሜትርና የጎዳና የዙር ውድድር መቀለ 70 እንደርታ ሁለት የዋንጫዎች ባለቤት መሆኑን የውድድሩ አስተባባሪ መምህር ጸሀየ አደም ገልጸዋል፡፡ ምርጥ የብስክሌተኞችና  ምርጥ አስልጣኞች የተዘጋጀላቸውን ሽልማት መውሰዳቸውን አስተባባሪው ተናግረዋል ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም