ሰላማችንን ለማስጠበቅ በጋራ መስራት አለብን - የበዓሉ ተሳታፊዎች

75
ኢዜአ ህዳር 29/2012  በአገር ደረጃ እየገጠመን ያለውን ችግር ለመፍታትና ሰላማችንን ለማስጠበቅ በጋራ መስራት አለብን ሲሉ የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን የተሳተፉ ሰዎች ገለጹ። የ14ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን "ሕገ-መንግስታዊ ቃል ኪዳናችን ለዘላቂ ሠላማችን" በሚል በኦሮሚያ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።   በዚሁ ወቅት በዓሉን ለማክበር ከተለያዩ የአገሪቷ አካባቢዎች የመጡ ተሳታፊዎች ለኢዜአ እንደተናገሩት በአንድነት አብሮ ለመኖር ሰላማችንን ማስጠበቅ አለብን ብለዋል። ሁሉም ሰው እንደ ኢትዮጵያዊ ባህል በመከባበርና በመፋቀር አብሮ መኖር እና ሰላማችን በራሳችን እጅ በመሆኑ በጋራ መጠበቅ አለብን ሲሉም ጠቁመዋል። ሰላም ከሌለ ማንም ሰው ተረጋግቶ መኖር እና መስራት እንደማይችል የጠቆሙት ተሳታፊዎቹ ለሁላችንም ሲባል ተፈቃቅሮና ተከባብሮ መኖር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። በተለይም ወጣቶች በስሜት ተገፋፍተው ለአደጋ መጋለጥ የለባቸውም፤ የራሳቸውንም ሆነ የቤተሰባቸውን ህይወትን ማናጋት የለባቸውምም ብለዋል። አሁን ያገጠመንን ችግር ለመፍታትም ሁላችንም የጋራ መፍትሄ ለማምጣት መስራት አለብን ሲሉ ተናግረዋል።          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም