በትራፊክ አደጋ ላይ ያጠነጠነ የንቅናቄ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

51
ኢዜአ ህዳር 27/2012 "እንደርሳለን" የተሰኘ በትራፊክ አደጋ ላይ ያጠነጠነ የንቅናቄ መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። 'እንደርሳለን' የተሰኘ በትራፊክ አደጋ ላይ ያጠነጠነ አገር አቀፍ የማህበረሰብ ንቅናቄ መድረክ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ እየተደረገ ነው። በመድረኩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የባለድርሻ አካላት ታድመዋል። በተሽከርካሪ አደጋና መንገድ ደህንንት ላይ ካተኮሩ ዝግጅቶች በተጨማሪ ጠንቃቃ አሽከርካሪዎችም ምስጋናና ዕውቅና ይሰጣቸዋል ተብሏል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም