የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አንድ ተማሪ ለአንድ ቤተሰብ መርሀ ግብር ጀመረ

73
ኢዜአ ህዳር 27 /2012  የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ያዘጋጀው አንድ ተማሪ ለአንድ ቤተሰብ ፕሮጀክት መርሃ ግብር ዛሬ በይፋ ጀመረ፡፡ በመርሀ ግብሩ ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ወቅት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያምን ጨምሮ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ማስተዋል ስዩም፣ የዩንቨርሲቲው ተማሪዎችና መምህራን፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና ጥሪ የተደረገላቸው የከተማው ነዋሪዎችም ተሳትፈዋል፡፡ በይፋ በተጀመረው መርሀ ግብር ዩኒቨርሲቲው በዘንድሮ ትምህርት ዘመን የተቀበላቸውን 5ሺህ የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ተማሪዎች በጎንደር ከተማ ነዋሪ የሆኑ ፈቃደኛ ቤተሰቦች የሚረከቡበት እንደሆነ ተመልክቷል።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም