‘’ ፕሮ ሆሊስቲክ አፍሪካ’’የተባለ የስፔን ድርጅት ለትግራይ ብስክሌት ስፖርት ድጋፍ አደረገ

62
ኢዜአ ህዳር 27 /2012 ዓም. ‘’ፕሮ ሆሊስቲክ አፍሪካ’’የተባለ የስፔን ድርጅት የትግራይ ብስክሌት ስፖርትን ለማጎልበት የመወዳደሪያ ብስክሌቶችና ተያያዥ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ ። ‘’ፕሮ ሆሊስቲክ  አፍሪካ’’ ያደረገው ድጋፍ  11 የማውንቴን ብስክሌቶች ከነ ሙሉ ተጓዳኝ እቃዎቹ ጋር መሆኑን ተገልፇል ። የትግራይ ክልል ብስክሌት ፌደሬሽን ምክትል ፕረዚዳንት አቶ ታደሰ ነጋሽ በርክክቡ ስነስርዓት ላይ እንደተናገሩት የተደረገው ድጋፍ በክልሉ ያለውን የማውንቴን ብስክሌት ስፖርት ከፍ ያደርገዋል ። ድጋፉ  ተተኪ ስፖርተኞች ለማፍራት የተጀመረው ፕሮጀክት ለማስፋት ትልቅ አቅም ይፈጥራልብለዋል። የፕሮ ሆሊስቲክ  አፍሪካ ድርጅት መስራችና አስተባባሪ ሚስተር ፓውሎ ሌሬስ በበኩላቸው በትግራይ ያለውን የብስክሌት ስፖርት በቁሳቁስ ብቻ ሳይሆን በቴክኒክና በአቅም ግንባታ መስክ ወደተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ይሰራል ብለዋል። ታዳጊ ስፖርተኞች ኢንተርናሽናል ልምድ ቀስመው በትላልቅ አህጉር አቀፍ ውድድሮች ተሳታፊ እንዲሆኑ ከፌደሬሽኑ ጋር በትብብር እንደሚሰሩ ተናግረዋል ። የክልሉ ወጣቶች ለብስክሌት ስፖርት ያላቸው ፍላጎት ጥሩ በመሆኑ በቱር ውድድር የዳገት፤ ሜዳ፤ ቁልቁለትና የቮላታ ቴክኒክ ልምዶች በማከፈል ጠንካራ ተፎካካሪ ስፖርተኞች ለማፍራት ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም