የጋምቤላ ፖሊስ ህጋዊነት የሌላቸው 101 ሞተር ሳይክሎች መያዙን ገለፀ

54
ህዳር 27/2012  በጋምቤላ ያለ ሰሌዳ ቁጥር ሲንቀሳቀሱና መንጃ ፈቃድ በሌላቸው ግለሰቦች ሲነዱ የነበሩ 101 ሞተር ሳይክሎች መያዙን የከተማዋ ፖሊስ ገለፀ ።
በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የትራፊክ አደጋ ቁጥጥር ስታቲስቲክስ ኦፊሰር ምክትል ኢንስፔክተር ታደለ አየለ ለኢዜአእንደገለፁት ሞተር ሳይክሎቹ የተያዙት አንዳንዶቹ ያለ መንጃ ፈቃድ ሲያሽከረክሩ ቀሪዎቹ ደግሞ የሰሌዳ ቁጥር ስለሌላቸው ነው ብለዋል ። በተደረገው ድንገተኛ ቁጥጥር  101 ሞተር ሳይክሎች የተያዙ ሲሆን ቁጥጥሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል ። ከተያዙት ሞተር ሳይክሎች መካከል 27ቱ የሰሌዳ  ቁጥር የሌላቸው ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ የመንጃ ፈቃድ በሌላቸው ግለሰቦች ሲሽከረከሩ የነበሩ ናቸው ። በተለይም በከተማዋ የሰሌዳ ቁጥር የሌላቸው ሞተር ሳይክሎች አደጋ አድርሰው የሚጠፉበት ሁኔታ መኖሩን ምክትል ኢንስፔክተሩ ጠቁመው ችግሩን ለመፍታት የትራፊክ ፖሊስ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በክልሉ የትራፊክ ፍሰትን ለማሳለጥና የሚደርሰውን አደጋ ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ምክትል ኢንስፔክተሩ ይህ ስራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል፡፡ በተለይም ባለፈው ወር በተደረገው የቁጥጥርና ክትትል ስራ ከ300 በላይ የግልና የመንግስት ተሸከርካሪዎች የሶስተኛ ወገን የመድህን ዋስትና ገዝተው እንዲለጥፉ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ በከተማዋ ብሎም በክልሉ የተሳለጠ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖርና በትራፊክ አደጋ የሚደርሰውን የሰው ሕይወትና የንብረት ውድመት ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ህብረተሰቡም የድርሻውን እንዲያበረክት ማበርከት ምክትል ኢንስፔክተር ታደለ ጥሪ አቅርበዋል ።      
 
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም