በትግራይ ደቡባዊ ዞን መኾኒ ከተማ የደረሰው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ

106
ኢዜአ ህዳር 26 ቀን 2012 ዓም  በትግራይ ደቡባዊ ዞን መኾኒ ከተማ ትናንት ሌሊት በደረሰው የእሳት አደጋ 2 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የራያ አዘቦ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ገለፀ ። የፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሓየሎም ረዳኢ ለኢዜአ እንደገለፁት የእሳት አደጋው ያጋጠመው ትናንት ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ላይ ነው የደረሰው ። የአደጋው መንስኤ የኤሌክትሪክ ገመድ እርስ በራሱ ተጠላልፎ በፈጠረው እሳት ሲሆን በከተማው የገበያ ቦታ ሁለት ሚሊዮን ብር የሚገመት ጉዳት አድርሷል ። በአደጋው የ56 ነጋዴዎች ዘይትና ጫማ ሙሉ በሙሉ ወድሟል ። ህብረተሰቡ ባደረገው ርብርብ በሌሎች መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ሱቆች ላይ ተጨማሪ አደጋ ሳያደርስ በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም