በክልሉ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራም ላይ ውይይት ነገ ይጀመራል

63
ኢዜአ ህዳር 26 ቀን 2012  በደቡብ ክልል በሚገኙ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በብልጽግና የፓርቲ መተዳደሪያ ደንብና ፕሮግራም ዙሪያ ከነገ ጀምሮ ውይይት እንደሚካሄድ የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የጽህፈት ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ ሜጎ ለኢዜአ እንደገለጹት ለሁለት ቀን በሚካሄደው የውይይት መድረክ እስከ ቀበሌ ባለው መዋቅር የሚገኙ አመራሮች ይሳተፋሉ። በመድረኩ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ፣ ፕሮግራምና፣ መሰረታዊ እሳቤዎች ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚካሄድ ኃላፊው አስታውቀዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም