በኮንጎ 5 ሺህ ሰዎች በኩፍኝ  በሽታ መሞታቸው ይፋ ሆነ

71

ኢዜአ፤ ህዳር 26/2012 በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በዚህ አመት በኩፍኝ በሽታ የሞቱ ሰዎች 5 ሺህ የደረሱ ሲሆን አብዛኞቹ ወጣቶችና ህፃናት መሆናቸውን የአለም ጤና ድርጅት ገለፀ፡፡

እአአ 2019 ከገባ ጀምሮ ከ2 መቶ 50 ሺህ ሰዎች በላይ  በበሽታው የተያዙ ሲሆን ህይወታቸው ካለፉት  ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ከአምስት አመት በታች የእድሜ ክልል የሚገኙ ህፃናት መሆናቸው የድርጅት መረጃ ያመለከተው።

በኮንጎ 26 ግዛቶች ላይ ያጋጠመው ተላላፊው የኩፍኝ በሽታን ለመከላከል የመጀመሪያው የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ መደረጉም ተገልጿ፡፡

ቀጣይ ዘመቻ የሚቀጥል ሲሆን በዓመቱ መጨረሻም ከ18 ሚሊዮን በላይ ሕፃናትን በመላው አገሪቱ የማዳረስ ዓላማ ያለው እንደሆነም ተጠቁሟል።

በዲሞክራቲክ ኮነጎ የኢቢላ በሽታ ተስፋፍቶ ህይወትን ለማዳን አለም አቀፍ ትኩረት በሳበበት ወቅት ሌሎች ጊዜ የማይሰጡ በሽታዎች ሊረሱ እንደማይገባ የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶክተር ማትስሶሶ ሞኢቲ ገልፀዋል፡፡

(ሲጂቲኤን አፍሪካ)