በትግራይ ዓመታዊ የብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር ላይ በሴቶች መቀሌ 70 እንደርታ ብቻ የዋንጫና የወርቅ

78
ኢዜአ ህዳር ር 25/12 ዓ/ም በሽሬ እንዳስላሴ ከተማ ላለፉት ስድስት ቀናት ሲካሔድ በሰነበተው የትግራይ ክልል ዓመታዊ የብስክሌት ሻምፒዮና ውድድር በሴቶች መቀሌ 70 እንደርታ የወርቅ ሜዳሊያና የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ ። ከህዳር 20 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በድምቀት በመካሄድ ላይ ባለው የብስክሌት ውድድር በሴቶች መካከል በተካሄደው የቡድን እሽቅድድም መቀሌ 70 እንደርታ የዋንጫና የወርቅ ሜዳሊያ ብቸኛ ተሸላሚ ሆኖ ማጠናቀቁን የውድድሩ አስተባባሪ መምህር ጸሃየ አደም ገልጸዋል። በከተሞችና በወረዳዎች መካከል በተደረገው ውድድርም ውቅሮ ከተማ አንደኛ በመሆን የዋንጫና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሲሆን ደጉዓ ቴምቤን ወረዳና ዓቢዪ ዓዲ ከተማ ደግሞ የብርና የነሃስ ሜዳሊያዎችን አግኝቷል። በቡድን በኮርስ “ቢ” የወንድ ክለቦች ውድድር ጉና ኃላፊነቱ የተወሰነ የንግድ ድርጅት የዋንጫና የወርቅ ሜዳልያ ተሸላሚ ሆኗል። ወልዋሎና ሳባ እምነበረድ ክለቦች ደግሞ ሁለተኛ እናሦስተኛ ደረጃዎችን በመያዝ  የብርናየነሓስ ሜዳሊያዎችን ወስደዋል ። የስፖርት አፍቃሪን ቀለብ ስቦ በነበረው የሴቶች ኮርስ “ኤ” የ30 ኪሎ ሜትር የቡድን የዙር ውድድር ደግሞ መስፍን ኢንጂኔሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ተቋም የወርቅ ሜዳሊያና የዋንጫ ባለቤት ሲሆን ትራንስ ኢትዮጵያና መሰቦ ሲሚንቶ ክለቦች ደግሞ የብርና የነሓስ ሜዳሊያዎች ባለቤት ሆነዋል ። በወረዳዎችና ከተሞች መካከል በተካሄደው የሴቶች የማውንቴን ብስክሌት ክርኖ ሜትር ውድድር ላይ ደጉዓ ተምቤን ወረዳ አንደኛ ፣ሽሬ እንዳስላሴ ሁለተኛ አብይ ዓዲ  ደግሞ 3ኛ ሆነው በማጠናቀቅ ሽልማታቸውን ወስደዋል ። በተመሳሳይ የወንዶች የማውንቴን ብስክሌት ክሮኖ ሜትር ወድድር ውቅሮ ከተማን የዋንጫና የወርቅን ተሸላሚ ሲሆን፣የሽሬ እንዳስላሴና አብይ ዓዲ ከተሞች ደግሞ የብርና የነሓስ ሜዳሊያዎችን ተቀብለዋል ።   በቡድን ደረጃ በተካሄደው የማውንቴን ብስክሌት ክሮኖ ሜትር በወንዶች ደስታ የአልኮል መጠጦች ፋብሪካ የወርቅና የዋንጫ አሸናፊ ሆኗል። የአዲግራትና የአድዋ ከተሞች የመጠጥ ውሃ አገልግሎቶች ደግሞ እንደየቅደም ተከተላቸው የብርና የነሃስ ሜዳሊያዎችን በማግኘት ውድድራቸውን አጠናቅቀዋል። በቡድን ኮርስ “ኤ” በወንዶችና በሴቶች ክሮኖ ሜትር ትራንስ የወርቅና የዋንጫ አሸናፊ ሲሆን፣በወንዶች መካከል በተካሄደው ውድድር ደግሞ ጉና ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የብር ሜዳሊያ ሲያገኝ፣መሰቦ ስሚንቶ ፋብሪካ ደግሞ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ የነሃስ ሜዳሊያ ተሸላሚ መሆኑን የውድድሩ አስተባባሪ ተናግረዋል ። በኮርስ “ኤ” በክሮኖ ሜትር ውድድር ላይ ወንዶች  በሰዓት 48 ነጥብ 64 ኪሎ ሜትር የበረሩ ሲሆን ሴቶች ደግሞ በሰዓት 42 ኪሎ ሜትር በመብረር የጋለ ፍክክር አሳይተዋል ። በዓመታዊ የብስክሌት ሻምፒዮናው 170 ተወዳዳሪዎች እየተሳተፉ ሲሆን ውድድሩ የፊታችን እሁድ ይጠናቀቃል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም