በአፍሪካ የትራንስፖርት አገልግሎት ለሴቶች፣ ህጻናትና አካል ጉዳተኞች ምቹ እንዳልሆነ ተገለጸ

54
ኢዜአ ህዳር 24 / 2012 ዓም በአፍሪካ የትረንስፖርት አገልግሎት ለሴቶች፣ ህጻናትና አካል ጉዳተኞች ምቹ እንዳልሆነ ተገለጸ። የትራንስፖርት ሚኒስቴር  ሴቶችን በትራንስፖርቱ ዘርፍ ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ መድረክ ከባለድረሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ አካሄዷል። የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በዚሁ ወቅት እንዳሉት በአፍሪካ አገራት በአጠቃላይ እና በተለይም ደግሞ በአገራችን ለሴቶች፣ ለህጻናትና ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የትራንስፖርት አገልግሎት አልተፈጠረም ብለዋል። በተለይም ሴቶች በትራንስፖርት ውስጥ ከሚደርስባቸውን ጥቃትና ትንኮሳ ተላቀው የሚፈልጉትን ተግባር እንዲከውኑ ለማስቻል ተቋሙ ከተለያዩ አገራትና በዘርፉ ጥሩ ተሞክሮ ካላቸው አገራት ልምድ በመቀመር  ችግሩን ለመፍታት እንደሚደሰራ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ከግማሽ በላዩን የህዝብ ቁጥር የሚሸፍነው የሴቶች ቁጥር በመሆኑም ካለባቸው ድርብ የስራ ሃላፊነት  አንጻር ግን የትራንስፖርት አቅርቦቱ አናሳ ነው ብለዋል። ይኸንን ችግር ለመፍታትም ተቋሙ ከአጋር አካላት ጋር ሲመክር ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ገልጸው፤ ከዚህም ተሞክሮዎችን ወስደን ወደ ስራ እንገባለን ብለዋል ሚኒስትሯ። አክለውም የዓለም የሀብት ኢንስቲትዩት(WRI) ካንትሪ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ኃይለስላሴ መድህን የብዝሃን ትራንስፖርት የሚጠቀሙ ሴቶች 90 በመቶ ያህሉ ጾታዊ ጥቃት እንደሚደርስባቸው ተቋሙ ያደረገው ጥናት ያመላክታል ብለዋል። ሴቶች በትራንስፖርት ኢንቨስትመንት ዘርፍም ያላቸው ተሳትፎ ምን ይመስላል የሚለውን ጥናት በማድረግ ለመደገፍና እርዳታ ለማድረግ ጭምር ይህ ውይይት ማስፈለጉን ገተልጸው፤ ሴቶች ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚችል የትራንስፖርት ዘርፍ ለመፍጠር ተሞክሮ መለዋወጡ አንድ እምርታ እንደሆነም አክለዋል። መድረኩ የተዘጋጀው በዓለም የሀብት ኢንስቲትዩት(WRI)፣ ፊሎን ኢኒሼቲቭና ትራንስፖርት ሚኒስቴር በመተባበር ነው።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም