ህገ-መንግስቱንና የፌዴራል ስርዓቱን ከአደጋ መጠበቅ ይገባል…ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል

91
ኢዜአ ህዳር 23/2012 ህገ-መንግስቱንና የፌዴራል ስርዓቱን ከማንኛውም አደጋ መጠበቅ አስፈላጊ እንደሆነ የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ገለጹ። የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያዘጋጀው የውይይት መድረክ በመቀሌ ከተማ እየተካሔደ ነው። ምክትል ርዕሰ-መስተዳደሩ በመድረኩ መክፈቻ ላይ ህገ-መንግስቱንና የፌዴራል ስርዓቱን ከስጋት መጠበቅ ያስፈልጋል ብለዋል። በውይይት መድረኩ ላይ ለተገኙት ተሳታፊዎች ምስጋና ያቀረቡት ምክትል ርዕሰ-መስተዳደሩ በመድረኩ የሚቀርቡ ሃሳቦች ለሃገሪቱ መፃኢ እድል የጎላ ፋይዳ እንደሚኖራቸው እምነታቸውን ገልጸዋል። የመድረኩ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል ዶክተር ሙሉጌታ ባካሎ በበኩላቸው በመድረኩ ላይ በሚቀርቡ ጥናታዊ ጽሁፎች መነሻነት ለሁለት ቀናት ውይይቱ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም