በጅማ ከተማ በህብረተሰቡ ጤና ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ የተረጋገጠ የቅቤና ማር ምርት ተወገደ

59
ኢዜአ ህዳር 22/2012 በህብረተሰቡ ጤና ላይ ጉዳት እንደሚያደርስ የተረጋገጠ ከ21 ቶን በላይ የምግብ ቅቤና የማር ምርት ዛሬ መወገዱን በኢትዮጵያ የምግብ፣ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ አስተዳደርና ቁጥጥር ባለስልጣን የጅማ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት ገለጸ። የተወገደው ምርት ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በህብረተሰቡ ጥቆማ የተገኘና ሁለት ሚሊዮን 800ሺህ ብር የሚገመት መሆኑን የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ በቃሉ አረጋ አስታውቀዋል። ምርቱ የተገኘው በጅማ ከተማ ውስጥ ሲሆን ለጤና ጎጂ መሆኑን በቤተ ሙከራ ምርመራ ከተጋገጠ በኋላ ነው ምርቱ የተወገደው። ድርጊቱ ወንጀል በመሆኑ በድርጊቱ የተጠረጠሩ ግለሰቦች በወቅቱ ተይዘው ጉዳያቸው በህግ አግባብ እንዲታይ ለሚመለከተው የፍትህ አካል  መተላለፉን ጠቁመዋል። የተወገደው  ቅቤና የማር ምርት ሰዎች ከተመገቡት ለካንሰር በሽታ የሚያጋልጥ ባዕድ ነገር የተቀላቀለበት መሆኑን  በምርመራ መረጋገጡን ኃለፊው አስታውቀዋል።፡ በቀጣይ ሳምንትም  ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸውና  ለጤና ጎጂ መሆናቸው የተረጋገጡ የታሽጉ የምግብ ምርቶች ለማስወገድ በዝግጅት ላይ እንዳሉም አመልክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም