ውህደት የፈጸሙት ፓርቲዎች ስምምነት ተፈራረሙ

64
ኢዜአ ህዳር 21/2012  ውህደት የፈጸሙት የኢህአዴግና አጋር ድርጅቶቹ ፓርቲዎች የስምምነት ፊርማ ተፈራረሙ። የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) አባል እና አጋር ድርጅቶች ብልፅግና ፓርቲን ለመቀላቀል በጉባዔያቸው ውሳኔ ሲያሳልፉ መቆየታቸው ይታወሳል። ብልፅግናን የተቀላቀሉት ፓርቲዎች ቁጥርም ስምንት ደርሷል። በዛሬው ዕለት የጋራ ስምምነቱን የተፈራረሙትም ውህደቱን ያጸደቁት ፓርቲዎች ሊቀ-መናብርት ናቸው። በስነ-ስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ብልጽግና ፓርቲ ኢትዮጵያን የሚያሸጋግራት ድልድይ ነው ብለዋል። በእውነትና ብቃት ላይ የተመሰረተ ስራ በመስራት ኢትዮጵያን ወደተሻለ ደረጃ እናደርሳታለን ሲሉም  ተናግረዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም