በተከፈለው መስዋዕትነት ብሔራዊ አንድነትን ያከበረ ፌዴራላዊ ሥርዓት ተገንብቷል..ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል

68
መቀሌ ሰኔ 15/2010 በተከፈለው መራራ መስዋእትነት እኩልነት ላይ የተመሰረተ ብሄራዊ አንድነትን ያከበረ ስርአት መገንባት መቻሉን የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል አስታወቁ፡፡ በየዓመቱ ሰኔ 15 የሚከበረው የሰማእታት ቀን በመቀሌ ሰማዕታት ሀወልት ቅጥር ግቢ  በደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ  ዛሬ ተከብሯል። ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ እንዳሉት በትጥቅ ትግሉ የተከፈለው መስዋእትነት በከንቱ አልቀረም ። በተከፈልው መስዋእትነት እኩልነት ላይ የተመሰረተ  ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ስርአት መገንባት መቻሉንም ተናግረዋል። ባለፉት አመታት በአገራችን የተመዘገበው ፈጣን እድገትም የመስዋእትነቱ ውጤት መሆኑን ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። በዓሉን ከመቀሌ ከተማ የተውጣጡ በርካታ ነዋሪዎች በደማቅ የሰልፍ ሥነ-ስርዓት አክብረውታል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም