ኢትዮጵያ ሳተላይት የምታመጥቅበት ዕለት በሶስት ቀናት ተራዘመ

79
ኢዜአ ህዳር 20/2012 ኢትዮጵያ ታህሳስ 7 ቀን 2012 ዓ.ም የምታመጥቀው ሳተላይት በአየር ሁኔታ አመቺነት የተነሳ ወደ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑ ተገለጸ። የቻይ ና ብሔራዊ ስፔስ ኤጀንሲ ከቻይና ሜትሮሎጂ ባገኘው መረጃ የኢትዮጵያን ሳተላይት ለማምጠቅ የተያዘው ህዳር 7 ቀን የአየር ሁኔታ ምቹ አለመሆኑ ታውቋል። በዚህ የተነሳም ሳተላይት የማምጠቁ ቀጠሮ በሶስት ቀናት ተራዝሟል። የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክትር ዶክተር ሰለሞን በላይ እንደገጹት፤ የአየር ሁኔታ ምቹ  አለመሆኑ ቀኑን ለማራዘም አስገድዷል። በቻይና የተሰራችውና 72 ኪሎ ግራም የምትመዝነው ሳተላይት በአካባቢ ጥበቃ፣ በግብርና እና በአየር ሁኔታ መረጃ ትሰጣለች። ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓም ከቻይና ቤጂንግ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትወነጨፈው የኢትዮጵያ ሳተላይት ከመሬት 700 ኪሎ ሜትር ርቃ ትቀመጣለች ነው የተባለው። ሳተላይቷ በዕለቱ ከማለዳው 12 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ነው ወደ ህዋ የምትጓዘው። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት በ2008 ዓም የተጀመረ ፕሮጀክት ነው አሁን እውን የሆነው።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም