ማዕከላዊ ኮሚቴው በብልፅግና ፓርቲ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ላይ ውይይት ጀመረ

84
ጅግጅጋ (ኢዜአ) ህዳር 17 ቀን 2012 የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ በብልጽግና ፓርቲ ፕሮግራምና መተዳደሪያ ደንብ ላይ ዛሬ መወያየት ጀመረ። የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በጅግጅጋ ከተማ የጀመሩት ውይይት ለሁለት ቀን እንደሚቆይ ተነግሯል። የፓርቲው ማዕከላዊ ጽህፋት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሀመድ ዑመር ለኢዜአ እንደገለፁት በዛሬው የውይይት መድረክ በብልጽግና ፓርቲ መተዳደሪያና ፕሮግራም ሰነድ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ይደረጋል። ከውይይቱ በኋላ ሰነዱ በአባላቱ ይጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመላክተዋል ። በማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በሰነዱ ላይ የተጀመረው ውይይት እስከ ፊታችን እሁድ ድረስ በአገር ሽማግሌዎች፣ በምሁራንና በሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች የሚካሄድ መሆኑንም ጠቁመዋል። የሶዴፓ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ትላንት ከብልፅግና ፓርቲ ጋር ለመዋሀድ መወሰኑ ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም