በደብረ ብርሃን ከተማ ከ7 ሺህ በላይ ሀሰተኛ የብር ኖቶች የተገኘባቸው ግለሰቦች ተያዙ

122
ኢዜአ ህዳር 15/ 2012  በደብረብርሃን ከተማ ከ7ሺህ ብር በላይ ሀሰተኛ ባለመቶ የብር ኖቶች ሲመነዝሩ ተደርሶባቸዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦችን መያዙን ፖሊስ አስታወቀ:: የከተማዋ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር ታየ ኃይለጊዮርጊስ ለኢዜአ እንደገለጹት ግለሰቦቹ ሊያዙ የቻሉት በህብረተሰቡ ጥቆማ  ነው። እነዚህ ግለሰቦች በከተማዋ ከተለያዩ ከሱቆች የሞባይል ካርዶች እና ሌሎች ሸቀጦችን በመግዛት ሲመነዝሩ እንደተደረሰባቸው አመልክተዋል። ግለሰቦቹ ተይዘው ሲፈተሹ በኪሳቸው 7ሺህ 1 መቶ ብር ባለ መቶ ብር ሀሰተኛ የብር ኖቶችና የሞባይል ካርዶች እንደተገኘባቸው ኮማንደር ታየ ገልጸዋል። ህብረተሰቡ ተመሳሳይ ህገ ወጥ ድርጊት ሲያጋጥመው ለፖሊስ በመጠቆም ወንጀልን በጋራ የመከላከል ባህሉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም