በኬንያ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 60 ደርሷል

56

ኢዜአ፤ ህዳር 15/2012 በሰሜናዊ ምእራብ ኬንያ እሁድ እለት ባጋጠመው ያልተጠበቀ ከባድ ዝናብ አመካኝነት የደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ  የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ ስልሳ ከፍ ማለቱን የኬንያ ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡

ባለፈው አርብ ኡጋንዳን የሚያዋስኑ የምእራብ ፖኮት ሃገራት ላይ ለሊት ላይ ባጋጠመው ጎርፍና መሬት መንሸራተት ድልድዮች በመፈራረሳቸው የአካባቢውን ነዋሪዎች እንቅስቃሴ ማስተጓጎሉ ተጠቅሷል፡፡

የምእራብ ፖኮት የመንግስት ባለስልጣናት እንዳሉት በመሬት መንሸራተት የሞቱት ሰዎች 53 የደረሱ ሲሆን ሰባት ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም፡፡

ሌሎች አምስት በመኪና ሲጓዙ የነበሩ ሰዎችና ሁለት እግረኞች በወንዝ ሙላት መወሰዳቸውም የመንግስት ባለስልጣናቱ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

“ባለፈው ምሽት ያጋጠው አደጋ አጋጥሞና ታይቶ የማያውቅ አሳዛኝ ገጠመኝ ነው” ሲሉ የምእራብ ፖኮት አስተዳዳሪ ጆን ክሮፕ ሎንያንጋፐው  ለአልጀዚራ ጠቅሰዋል፡፡

አደጋው ባጋጠመው ምሽት በተከታታይ ለ12 ሰአታት መዝነቡንም ነው አስተዳዳሪው ጨምረው የገለጹት፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም