በሰመራ ከተማ 9ኛው ሀገር አቀፍ የአብሮነት ቀን እየተከበረ ነው

112
ህዳር 15/2012 ዓ.ም ሰመራ ኢዜአ...... የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከአፋር ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው 9ኛው ሀገር አቀፍ የአብሮነት ቀን ዛሬ በሰመራ ከተማ እየተከበረ ነው ። በበዓሉ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርን ጨምሮ የአፋር ክልል ከፍተኛ አመራሮች ፣ ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ የሃገር ሽማግሌዎች ፣ የሃይማኖት አባቶችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። ለአንድ ቀን በሚከበረው በዓል ላይ የህዝቦችን አብሮነት የሚያጠናክሩ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል። የአፋር ወግሪሳ የባህል ቡድንና የወሎ ላሊበላ  ኪነት ቡድን በበዓሉ መክፈቻ ላይ ጣእመ ዜማዎችን  አቅርበዋል ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም