በኬንያ በደረሰ ጎርፍ አደጋ 29 ሰዎች ሞቱ

83
ህዳር 14/2012 በኬንያ በምዕራብ ፓኮት አውራጃ በደረሰው ከባድ የአየር ጠባይ ምክንያት ቢያንስ 29 ሰዎች ሞተዋል ፡፡ በናርኪሊያን እና በፓዋዋ መንደሮች ላይ ከባድ የመሬት መንሸራተት ዝናብ ባስከተለው አደጋ ነው ጉዳቱ የደረሰው ፡፡ የሀገሪቱ ባለስልጣናት መንደሮቹ በጎርፍ በመጥለቀለቃቸው ባሻገር መንገዶች የተዘጉ ሲሆን ቢያንስ አንድ ድልድይ እንደተወሰደም ጠቁመዋል ፡፡ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በአደጋው “ከልብ የመነጨ ሀዘን” እንደተሰማቸው ለተጎጂ ዘመድ እና ጓደኞች ገልጸዋል፡፡ ኡሁሩ ኬንያታ በንብረት እና በመሰረተ ልማት ላይ “ከፍተኛ ጥፋት” መድረሱን ገልፀው የሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት በነፍስ አድን ስራ ላይ እንዲሰማራ ትእዛዝ አስተላልፈዋል፡፡ እስካሁን ድረስ ከሞቱት መካከል ሰባት ልጆች መገኘታቸውን ባለስልጣናት ገልፀዋል ፡፡  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም