የአዲሱ ውህድ ፓርቲ ህገ ደንብ ጸደቀ

116
ኢዜአ፤ ህዳር 12/2012 የኢህአዴግ ምክር ቤት የአዲሱን ውህድ ፓርቲ ህገ ደንብ በሙሉ ድምጽ አጸደቀ፡፡
 
የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲ ግንባር /ኢህአዴግ/ ምክር ቤት ለሀሉት ቀናት ሲያካሄድ የነበረውን ስብሰባ አጠናቋል፡፡
 
በሁለተኛ ቀን ውሎው ዛሬ የአዲሱ ውህድ ፓርቲ ህገ ደንብ ላይ በጥልቀት ከመከረ በኋላ የተገኙት አባላት በሙሉ ድምጽ ማጽደቃቸውን ከኢህአዴግ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
 
በመጀመሪያ ቀን ውሎውም ምክር ቤቱ የፓርቲውን ውህደትና ፓርቲው ወደ ፊት የሚመራበት ፕሮግራም ላይ በመምከር አጽድቋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም