ኢትዮጵያ ሳተላይት ልታመጥቅ ነው

67
ኢዜአ ህዳር 12/2012   ኢትዮጵያ በመጪው ታህሳስ የመሬት ምልከታ ሳተላይት ወደ ህዋ ታመጥቃለች። ቻይና የተሰራችውና 72 ኪሎ ግራም የምትመዝነው ሳተላይት በአካባቢ ጥበቃ፣ በግብርና እና በአየር ሁኔታ መረጃ ትሰጣለች። ታህሳስ 7 ቀን 2012 ዓም ከቻይና ቤጂንግ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትወነጨፈው የኢትዮጵያ ሳተላይት ከመሬት 700 ኪሎ ሜትር ርቃ ትቀመጣለች ነው የተባለው። ሳተላይቷ በዕለቱ ከማለዳው 12 ሰዓት ከ21 ደቂቃ ነው ወደ ህዋ የምትጓዘው። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት በ2008 ዓም የተጀመረ ፕሮጀክት ነው አሁን እውን የሆነው። "በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ታሪክ ወሳኝ ምዕራፍ ነው" ያሉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ አገሪቱ ቴክኖሎጂ ገዥ ብቻ ሳትሆን ባለቤት መሆኗንም ያሳያል ብለዋል።        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም