ጉግል በፖለቲካ ማስታዎቂያዎች ላይ እገዳ ሊጥል  ነው

140
ኢዜአ፤ ህዳር 11/2012 ጉግል በመላ ዓለም በሚተላለፉ የፖለቲካ ይዘት ባላቸው ማስታዎቂያዎች ላይ እገዳ ሊጥል መሆኑን አስታወቀ። እርምጃው በምርጫ ዘመቻ ወቅት  ዩቲዩብና ጉግል መፈለጊያዎች መራጮችን ለማግኘት መጠቀም እንዳይቻል ያደርጋል ተብሏል። እገዳው በምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ወቅት ጉግልን ተጠቅሞ የመራጭ እድሜ ፣ ፆታ እና አድራሻን ለማወቅ የሚያስችሉ አሰራሮችን አይጨምርም ተብሏል። ጉግል ይህ እገዳ በአንድ በሳምንት ውስጥ በሀገረ-እንግሊዝ ተጀምሮ ወደ ሌሎች ሀገራት እንደሚቀጥል ገልጿል። እገዳው ከፖለቲካ ማስታወቂያዎች በተጨማሪ ሌሎች አፍራሽ መልዕክት በሚይዙ ማስታወቂያዎች ላይም እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል፡፡ የጉግል ማስታወቂያዎች ማናጀር ስኮት ስፔንሰር  የፖለቲካ ውይይት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አንዱ ወሳኝ ክፍል ስለሆነ ማንኛውም ሰው እንዳሻው የፖለቲካ ሃሳቦችን፣ተቃራኒ ሃሳቦችን ሊያሰራጭና ሊመራ አይገባም ብለዋል። " እርምጃ የሚወሰድባቸው የፖለቲካ ማስታወቂያዎች ውስን ቢሆኑም ወደፊት እንቀጥልበታለን" ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም