የአማራና ኦሮሚያ ክልሎችን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሰላም የምክክር መድረክ ተጀመረ

65

ኢዜአ፤ ህዳር 11/2012 የአማራና ኦሮሚያ ክልሎችን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሰላም የምክክር መድረክ  በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ።

የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር ባለመው በዚህ የውይይት መድረክ የሃይማኖት አባቶች አባ ገዳዎች የአገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች ታድመዋል።

መድረኩ በአገሪቷ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል።

ትናንትና የሁለቱ ክልሎች አክቲቪስቶችና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የተሳተፉበት ውይይት መካሄዱ ይታወሳል።

ውይይቱ ያተኮረው በሁለቱ ሕዝቦች ወቅታዊ ሁኔታ ላይ እንደነበር ትናንት ኢዜአ ዘግቧል።

ውይይቱ በተለይም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በክልሎቹ እያጋጠመ ያለው የሠላም መደፍረስ እያስከተለ ያለውን ከፍተኛ ጉዳት ማዕከል አድርጎ መካሄዱ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም