ዋሊያዎቹ የኮትዲቫር አቻቸውን አሸነፉ

82
ኢዜአ ህዳር 9/2012 የኢትዮጵያ ብሔራዉ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ከኮትዲቫር ጋር ባደረጉት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዋታ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸነፉ። ዋሊያዎቹ ጨዋታቸውን ያደረጉት ዛሬ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም  በፈረንጆቹ 2021 በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያን ለማለፍ ነው። ሁለተኛ የማጣሪያ ጨዋታቸውን ያደረጉት ዋሊያዎቹ  ጨዋታው እንደተጀመረ በኮትዲቫርዊው ሰርጂ ኦሪር አማካኝነት ተመርተው ነበር። ይሁን እንጂ ዋሊያዎቹ  በጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ በሱራፌል ዳኛቸውና ሽመልስ በቀለ አማካኝነት የአሸናፊነቱን ግብ ከመረብ አሳርፈዋል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን  ባለፈው ሳምንት   የአፍሪካ  ዋንጫ ማጣሪያ  የመጀመሪያ የምድብ ማጣሪያ  ጨዋታውን ከማዳጋስካር አቻው ጋር ያደረገ ሲሆን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት መሸነፉ ይታወሳል፡፡ ኢትዮጵያ ከኮትዲቫር፣ ኒጀር እና ማዳጋስካር የምድብ ማጣሪያ ጨዋታዋን እንደምታደርግ ይታወቃል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም