በሳህሊተ ምህረት አካባቢ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ከአነስተኛ የጭነት ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭቶ ቆሟል

66
ኢዜአ ህዳር 9/2012  ከጦር ኃይሎች ሲኤምሲ የባቡር ሃዲድ በተለምዶ ሳህሊተ ምህረት በሚባለው አካባቢ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ከአንድ የአነስተኛ የጭነት ተሽገርካሪ ጋር ተጋጭቶ መቆሙ ተነገረ። የአይን እማኞች ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የመለያ ታርጋ ቁጥሩ 170881-አዲስ አበባ የሆነ አነስተኛ የጭነት ተሽከርካሪና የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ሳሊተ ምህረት አካባቢ የግጭት አደጋ ደርሶባቸዋል። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓትም ተሽከርካሪዎች እንደቆሙ ናቸው። ስለደረሰው ጉዳትና ስለአደጋው መንስኤ ከሚመለከተው የፖሊስ አካል የተጣራ መረጃ ስናገኝ እናቀርባለን።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም