አቶ ያረጋል አይሸሹም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

117
አሶሳ ኅዳር  9 ቀን 2012 የቀድሞው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ያረጋል አይሸሹም አረፉ፡፡ አቶ ያረጋል ከአባታቸው ከአቶ አይሸሹም ብርሃኔ ና ከእናታቸው ከወይዘሮ ሽታዬ ይማም በ1961 በድባጤ ከተማ ተወለዱ፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ በድባጤ ሚሽን ትምህርት ቤት ፣ሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በቻግኒ ተከታትለዋል፡፡ በኮተቤ መምህራን ማሰልጠኛ ኮሌጅ በዲፕሎማ ከተመረቁ በኋላ በቀድሞው ባሌ ክፍለ ሃገር በመምህርነት አገልግለዋል፡፡ ክልሉን በተለያዩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት ያገለገሉት አቶ ያረጋል በተለይ ከ1987 እስከ 2002 ድረስ የክልሉ አራተኛው ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ባገለገሉበት ወቅት ለክልሉ ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና ለውጥ መሥራታቸው የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል፡፡ ከ2002 ጀምሮ እስከ 2007 የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልነት እንዲሁም ከ2002 እስከ 2005 የፌደራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ትናንት ምሽት በገጠማቸው ድንገተኛ ሕመም ከዚህ ዓለም  በሞት የተለዩት  አቶ ያረጋል የአንድ ሴትና የሶስት ወንድ ልጆች አባት ነበሩ፡፡    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም