ሉሲዎቹ በሴካፋ ዛሬ የመጀመሪያ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ

98
ኢዜአ ህዳር 7/2012 የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሉሲዎቹ በሴካፋ ዋንጫ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ። የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የሴቶቹ የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድሮች(ሴካፋ) ትናንት የተጀመረ ሲሆን በመክፈቻ ቀኑም ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል። በአሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው የሚመራው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን(ሉሲዎች) አባላትም ዝግጅታቸውን ሲያደርጉ ቆይተው ወደ ታንዛንያ አቅንተዋል። ትናንት በተደረጉ የምድብ አንድ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታዎችም ቡሩንዲ ዛንዚባርን 5 ለ 0 አሸንፋለች። እንዲሁም አስተናጋጇ አገር ታንዛንያ ከደቡብ ሱዳን ጋር የተጫወቱ ሲሆን በታንዛንያ 9 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል። የምድብ ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥለው የሚደረጉ ሲሆኑ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከኬንያ አቻው ጋር ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ይጫወታል። የዩጋንዳ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ደግሞ ከጅቡቲ ጋር ከቀኑ በ10:00 ሰዓት የሚጫወቱ ይሆናሉ። ዘንድሮ ለ4ኛ ጊዜ የሚካሄደው የመካከለኛውና ምስራቅ አፍሪካ የሴቶች ዋንጫ በታንዛንያ አዘጋጅነት ነው የሚካሄደው።   በዚህም በአጠቃላይ ስምንት የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ አገራት ይሳተፋሉ።   የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድንም በምድብ ሁለት ከጅቡቲ፣ ኬንያና ዩጋንዳ ጋር መደልደሉ ይታወቃል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም