በታላቁ ሩጫ ውድድር በሴቶች አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው በወንዶች አትሌት በሪሁ አረጋዊ አሸነፉ

85
ኢዜአ  ህዳር  7/201 2ዘንድሮ ለ19ኛ ጊዜ የተካሄደው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ በማድረግ በደማቅ ስነ ስርአት ተከናውኗል። በውድድሩ በሴቶች አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው በአንደኝነት ስታጠናቅቅ አትሌት ፅጌ ገብረስላሴና ዓለም ንጉስ ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነዋል። በወንዶች ደግሞ አትሌት በሪሁ አረጋዊ አንደኛ ሲወጣ አንድአምላክ በልሁ ሁለተኛ እንዲሁም ገመቹ ዳዳ ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል። ውድድሩ የተካሄደው መነሻና መድረውን መስቀል አደባባይ በማድረግ ስታድየም፣ ሜክሲኮ፣ ባልቻ ሆስፒታል፣ ጎማ ቁጠባ፣ በዋቢ ሸበሌ፣ ብሔራዊ ቴአትር፣ ሐራምቤ ሆቴል፣ ፍልውሃ፣ ቤተ-መንግስት፣ ካዛንችስ፣ ዑራኤል እና ባምቢስን በማካለል ነው። ውድድሩ ላይ 45 ሺህ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን ኬኒያዊቷ አትሌት ሄለን ኦቢሪ በክብር እንገድነት ስትገኝ በርካታ ታዋቂ ኢትዮጵያዊያን አስሌቶችም በስፍራው ተገኝተዋል።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም