ለሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ታዛቢነት የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች ስልጠና እየወሰዱ ነው

89
አዲስ አበባ ህዳር  7/2012 ለሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የምርጫ ሂደት የሚታዘቡ የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች በሃዋሳ ስልጠና እየወሰዱ ነው። በስልጠናው ላይ የተሳተፉት ከሁሉም ክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ 150 የሲቪክ ማህበራት ተወካዮች ናቸው። የሲቪክ ማህበራት ድርጅቶች የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ቡድን መሪ ወይዘሮ ብሌን አስራት እንደተናገሩት፤ ስልጠናው የምርጫው ሂደት ከሕገ-መንግሥቱ ፣ ከአዲሱ ምርጫ አዋጅና ከዓለም አቀፍ ህጎች አኳያ ታዛቢዎቹ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ነው። ስልጠናው ነገ የሚጠናቀቅ ሲሆን ታዛቢዎቹ በቀጣይ በሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ላይ በቋሚነት እየተንቀሳቀሱ የሚታዘቡ ይሆናል። በሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ከ300 በላይ የምርጫ ታዛቢዎች ወደ ሃዋሳ ለታዛቢነት ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ለህዝበ ውሳኔው የመራጮች ምዝገባ ትናንት የተጠናቀቀ ሲሆን የድምጽ መስጠት ሂደቱ የፊታችን እሮብ ህዳር 10 ቀን 2012 ዓ.ም የሚካሄድ ይሆናል።        
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም