የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድር እየተካሄደ ነው

117
አዲስ አበባ ህዳር  7/2012 19ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ  እየተካሄደ ነው:: በዘንድሮው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 45 ሺህ ተወዳዳሪዎች የተገኙ ሲሆን ከተለያዩ አገሮች የተጋበዙ አትሌቶችም ተሳታፊ ናቸው። የአምስት የተለያዩ ሀገራት አትሌቶች የውድድሩ ተሳታፊዎች መሆናቸውም ተነግሯል። ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ ከኬኒያ፣ ቦትስዋና፣ኡጋንዳና ኤርትራ የመጡ አትሌቶች ውድድራቸውን እያደረጉ ነው። ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ፣ አትሌት ብርሃኔ አደሬ፣ አትሌት ገዛኸኝ አበራን ጨምረው ኬኒያዊቷ አትሌት ሄለን ኦቢሪ በክብር እንግድነት ተገኝተው ውድድሩን አስጀምረዋል። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በዓለም ከሚካሄዱ የጎዳና ላይ ውድድሮች አንዱ ሆኗል። ዘንድሮም ለ19ኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን 45 ሺህ ተሳታፊዎቹን እያወዳደረ ይገኛል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም