የህግ ታራሚዎች በይቅርታ መለቀቃቸውን እንደግፋለን -የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች

73
አዲስ አበባ ሰኔ 13/2010 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ መለቀቃቸው ሰላምና አንድነትን የሚያመጣ በመሆኑ  እንደሚደግፉት ኢዜአ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል ወይዘሮ ፈትለወርቅ ድንቁ "ይቅርታ ማድረግ ሀገራዊ መግባባትን ለማምጣት ትልቅ አማራጭ ነው" ብለዋል። ሌላው አስተያየት ሰጪ አቶ ይፍሩ ታመነ ቀደም ሲል ሲታሰሩ በነበሩ ሰዎች መበራከት ምክንያት በሀገራቸው ተስፋ ቆርጠው እንደነበር ጠቅሰው፤ አሁን ለታራሚዎች የተደረገው ይቅርታ ትልቅ ተስፋ እንሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ የህግ ታራሚዎች በይቅርታ መለቀቃቸው ሀገሪቷን ወደ ተሻለ የእድገት ጎዳና  ይወስዳታል ያሉት ደሞ አቶ ይርጋ ጣሎ ናቸው። ሌላው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ አቶ ፍጹም ብስራት ደግሞ ለታራሚዎች ይቅርታ መደረጉ ሀገራዊ መግባባትን ስለሚያመጣ ሊደገፍ እንደሚገባ ገልጸው፤ ታራሚዎችም ከህብረተሰቡ ጋር ሲቀላቀሉ ለሰላምና ለአንድነት ዘብ እንዲቆሙ ጠይቀዋል። ወደ  እድገት የሚወስደውንና ምክንያታዊ የሆነውን የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የለውጥ እርምጃዎችን እንደሚደግፉም ነው አቶ ፍጹም የተናገሩት።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም