ምዕራብ ጎንደርና ገዳሪፍ በጸጥታና ሕገ ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል ተስማሙ

76
ኅዳር 5 / 2012 የምዕራብ ጎንደር ዞንና የሱዳኑ ገዳሪፍ ግዛት በጸጥታና ሕገ ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል በጋራ ለመስራት ተስማሙ። ስምምነቱን የተደረሰው በዞኑና በግዛት ሥር ከሚገኙት ዲንደር፣ የባሶንዳ ፣የምስራቅ ገላባትና ቡረሻ ዞኖች አስተዳደሮች ጋር መሆኑን አስተዳደሩ አስታውቋል። የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የሕዝብ ሰላምና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው ለኢዜአ እንደገለጹት ስምምነቱ በፀጥታ ለማስከበርና ሕገ-ወጥ ድርጊትን በመከላከልየጋራ ሰላምና ደህንነትን ለማስጠበቅ ያስችላል። በዚህም ኮንትሮባንድን፣ ሕገ-ወጥ የሰዎችና የጦር መሣሪያዎችን ንግድ፣ የአደንዛዥ እፅ ዝውውር እንዲሁም ስርቆት ለመከላከል እንደሚያስችል አስረድተዋል። በተጨማሪም ከሁለቱ አገሮች በወንጀል የሚፈጸሙ ግለሰቦችን አሳልፎ ለመስጠት እንደሚረዳ ኃላፊው  ገልጸዋል። የስምምነቱን  አፈጻጸም የሚከታተል ኮማንድ ፖስት በማቋቋም ክትትልና ቁጥጥር እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡ በአማራ ክልል የሚገኘው የምዕራብ ጎንደር ዞን ከተጎራባቹ የሱዳን ገዳሪፍ ግዛት ጋር  የሚዋሰነው 400 ኪሎ ሜትር ወሰን አለው።            
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም