በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር እየተወያዩ ነው

66
ህዳር 4/2012 በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በመወያየት ላይ ናቸው። በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ነው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር እየተወያዩ ያሉት። ውይይቱ በሠላምና ጸጥታ ጉዳዮች፣ የሁለቱ ክልሎች ህዝቦችና አንድነትን ማጠናከር እና ከሌሎችም የአገሪቱ ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በመሆን የኢትዮጵያን አንድነት መጠበቅ ላይ ትኩረቱን አድርጓል። ውይይቱን የሚመሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲሆኑ ከፖለቲካ ፓርቲዎቹ ባሻገር የሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮችም ታድመዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም