የአሜሪካ ባለሀብቶት ልዑካን ቡድን ዓርባ ምንጭ ገባ

53
ኅዳር 3 ቀን 2012  ''ስማርት ቪሌጅ'' የተሰኘ የአሜሪካ ባለሀብቶች ልዑካን ቡድን ዛሬ ዓርባ ምንጭ ገባ፡፡ ቡድኑ ዓርባ ምንጭ ኤርፖርት ሲደርስ የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ፣ የዓርባ ምንጭ ከተማ ከንቲባ አቶ ሰብስቤ ቡናቤ፣ ከፍተኛ አመራሮችና የአገር ሽማግሌዎች አቀባበል አድርገውለታል፡፡ የጋሞ ዞን አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አሰግድ ተረፈ ለኢዜአ እንደገለጹት ቡድኑ በከተማዋ የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት ያደርጋል። ቡድኑ የድርጅቱን መስራችና ፕሬዚዳንት እንዳካተተና በቆይታውም በከተማዋ በመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ዘርፍ ለመሰማራት በሚቻልበት መንገድ ላይ  ይመክራል ብለዋል። ከቡድኑ ጋር በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍጹም አረጋ ወደ ከተማዋ ገብተዋል። ዓርባ ምንጭ የኢኮ ቱሪዝም ልማት ተመራጭ  አካባቢ መሆኑ ይታወቃል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም