በወላይታ ዞን ጅብ የሦስት ሕጻናትን ሕይወት አጠፋ

49
ሶዶ ህዳር 3 /2012  በወላይታ ዞን ጅብ ባደረሰው ጉዳት የሦስት ሕጻናት ሕይወት ሲጠፋ በሌላ አንድ የሁለት ዓመት ልጅ ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደረሰ። የወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፖሊስ እንዳስታወቀው በህጻናቱ ላይ የሞትና የአካል ጉዳት የደረሰው በወረዳው "ኮዶ ጋውሊያ" በተባለ የገጠር ቀበሌ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት አሳቻ ሰዓታት ጠብቆ የመጣ ጅብ ባደረሰው ጥቃት ነው። ጅቡ ባደረሰው ጥቃት ሦስት ህጻናት ሕይወታቸውን ሲያጡ በአንዲት የሁለት ዓመት ልጅ ላይ ጉዳት መድረሱን የወረዳው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ስምኦን ጣዲሶ ተናግረዋል። በቀጣይ ጅቡ መሰል ጥቃቶችን እንዳያደርስ ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበል እርምጃ እንደሚወሰድ አመልክተዋል።      
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም